ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ የናይጄሪያን የፔትሮሊየም ምርቶች ውጪ ንግድ በሰባት እጥፍ አሳደገ

ሰብስክራይብ

ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ የናይጄሪያን የፔትሮሊየም ምርቶች ውጪ ንግድ በሰባት እጥፍ አሳደገ

እ.ኤ.አ በ2026 ሁለተኛ ሩብ ዓመት የናይጄሪያ የባሕር የፔትሮሊየም ውጤቶች ጭነት በቀን በአማካይ 561 ሺህ በርሜል ደርሶ፤ በ2023 ከተመዘገበው በቀን የ79 ሺህ በርሜል ዓመታዊ አማካይ ጋር ሲነጻጸር የሰባት እጥፍ እድገት አሳይቷል ሲል የአሜሪካ የኢነርጂ መረጃ አስተዳደር ገልጿል።

የዳንጎቴ ማጣሪያ ተፅዕኖ

ለዚህ ዕድገት ዋነኛው ምክንያት እ.ኤ.አ 2024 ሥራ የጀመረው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ነው። የማጣሪያው ምርት እያደገ መምጣቱ ለናይጄሪያ ሁለት ትልልቅ ስኬቶችን አስገኝቷል፦

የተቀነባበሩ የነዳጅ ውጤቶችን ከውጭ ማስገባትን ቀንሷል፣

የሀገር ውስጥ አቅርቦትና የውጭ ንግድ አቅምን አሳድጓል።

በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል በተፈጠሩ የእንቅስቃሴ መስተጓጎሎች ምክንያት ለአማራጭ የነዳጅ አቅርቦቶች ያለው ፍላጎት በመጨመሩ፤ አጠቃላይ የፔትሮሊየም ውጤቶች ንግድን እንዳሳደገ ተቋሙ ገልጿል።

ቁጥሮቹ በጥልቀት ሲታዩ

በናይጄሪያ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ጭነት እ.ኤ.አ በ2026 ሁለተኛ ሩብ ዓመት በቀን ወደ 211 ሺህ በርሜል አድጓል፤ ይህም ከ2025 በቀን 81 ሺህ እና ከ2023 በቀን 33 ሺህ በርሜል ጭማሪ አሳይቷል።

የባሕር የነዳጅ ምርቶች እ.ኤ.አ ከ2023 ዕለታዊ 400 ሺህ በርሜል፤ በ2026 ሁለተኛ ሩብ ዓመት በቀን ወደ 130 ሺህ በርሜል ቀንሷል።

እነዚህ ቁጥሮች ናይጄሪያ የተጣሩ የፔትሮሊየም ውጤቶችን በራስ የመሸፈን አቅሟ እያደገ መምጣቱን ያመላክታሉ።።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0