ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል በምዕራባውያን የታሪፍ ጫና መኻል ግንኙነታቸውን እና የደቡባዊ ዓለም ትብብርን ለማጠናከር ተስማሙ
ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል በምዕራባውያን የታሪፍ ጫና መኻል ግንኙነታቸውን እና የደቡባዊ ዓለም ትብብርን ለማጠናከር ተስማሙ
ሁለቱ ሀገራት በፕሪቶሪያ ያካሄዱትን 8ኛውን የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ያጠናቀቁ ሲሆን አዳዲስ ስምምነቶችንም ተፈራርመዋል። ይህም በምዕራባውያን ገበያዎች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና በብሪክስ፣ በቡድን 20 ሀገራት እንዲሁም በሕንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የውይይት መድረክ ማዕቀፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያደርጉት ጥረት አካል መሆኑን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሁለቱ ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን የሚጋፉ ፖለቲካዊ መነሻ ባላቸው ታሪፎች ኢላማ እንደሆኑ የጠቆሙት የብራዚል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ፤ ይህ ይበልጥ ለመቀራረብና ግልጽ የሆነ ትብብር ለመፍጠር የጋራ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ማድረጉን ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ፤ የሁለቱን ሀገራት አጋርነት ስትራቴጂካዊ እሴት ያመላከቱ ሲሆን ዓመታዊ የንግድ ልውውጣቸው 2 ቢሊዮን ዶላር መድረሱንና በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ገበያዎች በኩል ሰፊ የገበያ ዕድሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
የሁለትዮሽ ትብብርን ማሳደግና የደቡባዊ ዓለም አጋርነትን የማጠናከር ዓላማ ያላቸው አዳዲስ የመከላከያ፣ የጤና፣ የሳይንስ፣ የትምህርት፣ የስፖርት፣ የኢነርጂ እና የማዕድን ዘርፍ ስምምነቶች ፈርመዋል።
ለበለጠ መረጃ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ታቦ ማክዋክዋ ያዘጋጀውን ሙሉ ዘገባ ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X