የአናዳ ወረርሽኝ በትንሹ የ50 ሕፃናትን ሕይወት መቅጠፉን ተከትሎ የናይጄሪያ መንግሥት የቁጥጥር እርምጃዎችን ጀመረ

ሰብስክራይብ

የአናዳ ወረርሽኝ በትንሹ የ50 ሕፃናትን ሕይወት መቅጠፉን ተከትሎ የናይጄሪያ መንግሥት የቁጥጥር እርምጃዎችን ጀመረ

የሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ ግዛት አስተዳደር፤ ሥርጭቱ የከፋ ደረጃ ላይ የደረሰውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎች እንዲፋጠኑ ጥሪ ማቅረቡን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሕግ አውጪ አካላት አሁን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች በቂ አይደሉም በማለት፤ መንግሥት የግዛቱን የጤና ጥበቃ ሕግ ወደ ተግባር እንዲያስገባ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ይህ ቀውስ በአካባቢው ከተከሰቱት እጅግ አደገኛ ወረርሽኞች አንዱ ሲሆን በስድስት አካባቢዎች ተሠራጭቷል።

አናዳ ምንድን ነው?

አናዳ ልብና የነርቭ ሥርዓትን የሚያጠቁ መርዛማ ነገሮችን የሚያመነጭ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ነው። በናይጄሪያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት በቂ ክትባት ያላገኙ በመሆናቸው፤ ወረርሽኙ በፍጥነት ሊስፋፋ እንደሚችል መገናኛ ብዙኃን ጠቁመዋል።

የካኖ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ጄነራል መሐመድ አዳሙ ስለ ወቅታዊው ወረርሽኝ የሰጡት ገለጻ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0