ሺ ጂንፒንግ በ10 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብፅ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
17:04 26.08.2026 (የተሻሻለ: 17:14 26.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሺ ጂንፒንግ በ10 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብፅ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በነሃሴ ወር መጨረሻ በግብፅ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ቻይና እና ግብፅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩበት 70ኛ ዓመት ጋር የሚገጣጠም እና ለሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እድገት ልዩ ትርጉም ያለው ነውም ብለዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ሺ ጂንፒንግ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ከግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ ጋር ይመክራሉ።
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ፤ ቤጂንግ በጉብኝቱ የሚከተሉት ጉዳዮች ይሳካሉ ብላ ትጠብቃለች፦
▪ የቆየውን ወዳጅነት ማጠናከር፣
▪ የጋር ድጋፎችን የበለጠ ማሳደግ፣
▪ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማስፋፋት፣
▪ በቻይና እና ግብፅ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ መክፈት እንዲሁም ለቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላምና መረጋጋት አስተዋፅኦ ማበርከት።
ቪዲዮው እ.ኤ.አ በ2018 በቤጂንግ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም ጉባኤ ወቅት የግብፅ ፕሬዚዳንት በቻይና ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X