የኬንያ ፍርድ ቤት ለፕሬዝዳንታዊ ዕጩነት የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ መስፈርት ሰረዘ - የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን

ሰብስክራይብ

የኬንያ ፍርድ ቤት ለፕሬዝዳንታዊ ዕጩነት የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ መስፈርት ሰረዘ  - የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን

የከፍተኛው ፍርድ ቤት መስፈርቱን ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጉን ተከተሎ፤ ለፕሬዝዳንትነት፣ ለካውንቲ ገዢነት ወይም ለፓርላማ ወንበሮች ለመወዳደር የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ከእንግዲህ አስፈላጊ አለመሆኑን የምርጫ ኮሚሽኑ ኃላፊ አን ንደሪቱ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል።

ከኬንያውያን ዜጎች መካከል የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸው ከአራት በመቶ ያነሱ መሆናቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነሯ፤ ፍርድ ቤቱ መስፈርቱን አድሏዊ ሆኖ አግኝቶታል ሲሉ አብራርተዋል።

ቁልፍ ነጥቦች፦

◻ የዲግሪ መስፈርቱ እ.ኤ.አ በ2011 በወጣው የምርጫ ሕግ የተካተተ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 ውድቅ ከመደረጉ በፊት በ2013፣ 2017 እና 2022 ምርጫዎች ሥራ ላይ ውሎ ነበር።

◻ የኬንያ ፕሬዚዳንቶች የተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ነበሯቸው። ሙአይ ኪባኪ፣ ኡሁሩ ኬኒያታ እና ዊሊያ ሩቶ ዲግሪ የያዙ ሲሆን ጆሞ ኬንያታ እና ዳንኤል አራፕ ሞይ ግን አልነበራቸውም።

◻ ንደሪቱ ኮሚሽኑ ለተመረጡ የሕዝብ ኃላፊነቶች ግልጽ የሆነ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ መስፈርት እንዲያወጣ ፓርላማውን ለመጠየቅ ማቀዱን ጠቁመዋል።

◻ ኬንያ ለፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የማይጠይቁ እንደ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኡጋንዳ ያሉ ሀገራትን ተቀላቅላለች።

◻ ለ2027 ምርጫ ዕጩዎች ትውልደ ኬንያዊ መሆንን ጨምሮ ሌሎች ሕገ-መንግሥታዊ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

የኬንያ ገለልተኛ የምርጫ እና የድንበር ኮሚሽን እ.ኤ.አ ከ2022ቱ ምርጫ በፊት የምርጫ ሂደቱን ሲያሳይ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0