የመገጭ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ከ17 ዓመት መጓተት በኋላ ሊጠናቀቅ እንደተቃረበ ተገለጸ
15:34 26.08.2026 (የተሻሻለ: 16:09 26.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የመገጭ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ከ17 ዓመት መጓተት በኋላ ሊጠናቀቅ እንደተቃረበ ተገለጸ
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ዙሪያ የሚነባው የመገጭ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት 94% እንደደረሰ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ግድቡ በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የያዘ ሲሆን፣ ከ9.4 ሚሊዮኑ የዋና ግድብ ሙሌት ውስጥ 8.25 ሚሊዮኑ ተሞልቶ ቀሪው 1.15 ሚሊዮን ሜትር ኪዮብ ውሃ ሙሌት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሥራዎች፦
▪ የግድቡ ትርፍ ውሃ ማስወጫ፣
▪ የመስኖ ውሃ መቆጣጠሪያ ሲቪል ሥራ፣
▪ የመስኖ ውሃ ማስወጫ መጠንና ሃይል መቆጣጠሪያ፣
▪ ለጎንደር ከተማ ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚሆን ውሃ ማስወጫ ቱቦ እና መቆጣጠሪያ ገጠማ።
ፕሮጀክቱ በ2.4 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ወጪ በ2001 ዓ.ም ነበር የተጀመረው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X