የሩሲያ የኢኮኖሚ ጥንካሬ አሜሪካ መሩ የአትላንቲክ ሥርዓት መሸነፉን ያሳያል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የኢኮኖሚ ጥንካሬ አሜሪካ መሩ የአትላንቲክ ሥርዓት መሸነፉን ያሳያል - ባለሙያ
የሩሲያ የኢኮኖሚ ጥንካሬ አሜሪካ መሩ የአትላንቲክ ሥርዓት መሸነፉን ያሳያል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.08.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የኢኮኖሚ ጥንካሬ አሜሪካ መሩ የአትላንቲክ ሥርዓት መሸነፉን ያሳያል - ባለሙያ

​ሩሲያ፤ በምዕራባውያን ማዕቀብ ቢጣልባትም እንዲሁም ከዩክሬን እንዲያውም አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይን ጨምሮ ከአጠቃላዩ የአትላንቲክ የጋራ ደህንነት ሥርዓት ጋር ረጅም ጊዜ የወሰደ ወታደራዊ ፍልሚያ ውስጥ ብትገኝም፤ ኢኮኖሚዋ መጠኑን ጠብቆ መቀጠል ብቻ ሳይሆን ዕድገት ላይ ነው ሲሉ ቱርኳዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ሃካን ቶፕኩሩሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

 

​"ሩሲያ ከመላው የኔቶ ጥምረት ጋር እያደረገች ያለችውን የውክልና ጦርነት ተቋቁማ፤ ኢኮኖሚዋ በዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ለአትላንቲክ ሥርዓት የማንቂያ ደወል እና ድክመቱን የሚያሳይ ነው" ሲሉ ቶፕኩሩሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

​አሜሪካ መሩ የአትላንቲክ ሥርዓት ቀደም ብሎ መሸነፉን እና አሁን ሽንፈቱን ለመሸፈን መንገድ በመፈለግ ላይ ይገኛልም ብለዋል።

​ሩሲያ በበኩሏ የሀገር ውስጥ ገበያዋን በማስፋፋት ላይ ትኩረት ማድረጓ፤ በውጭ ንግድ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ተጽዕኖ ለመቀነስ እና የኢኮኖሚ ሀብቷን በጥንቃቄ ለመጠቀም አስችሏታል ሲሉ ባለሙያው አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0