ሩሲያ በሱዳን ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች እንዳይጣሉ ተቃወመች
08:31 26.08.2026 (የተሻሻለ: 08:34 26.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ በሱዳን ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች እንዳይጣሉ ተቃወመች
የአውሮፓ ኀብረት የወርቅ ገቢ ንግድ እገዳ እና የአሜሪካ የፋይናንስ እርምጃዎችን ጨምሮ ነባር ማዕቀቦች ቀድሞውኑ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደሩ እንደሆነ እና የመጨረሻው ጉዳት ተራው የሱዳን ዜጋ ላይ እንደሚያርፍ በተመድ የሩሲያ ተወካይ ቫሲሊ ነቤንዚያ አስታውቀዋል።
ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሚደረጉ የብድር፣ የፋይናንስ እና የቴክኒክ እርዳታዎች እገዳን የሚያካትቱት የዋሽንግተን መጠነ ሰፊ ማዕቀቦች ተቀባይነት የሌላቸው እና በሱዳን መንግሥት ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ እርምጃ ናቸው ብለዋል።
አሜሪካ በሱዳን ዳርፉር ላይ ብቻ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ወደ መላ ሀገሪቱ ለማስፋፋት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሀሳብ ማቅረቧን፤ በአፍሪካ ጉዳዮች የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ገልጸዋል።
በግጭቱ ድሮን መጠቀም የሰብዓዊ ሕግ ጥሰት ነው ሲሉም የኮነኑ ሲሆን ለሱዳን ጦርም ሆነ ለፈጣኖ ደራሽ ኃይሎች የሚደረገው ድጋፍ የጦርነቱ ዋነኛ አባባሽ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል።
የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ሁሉም ሀገራት ለተዋጊ ወገኖች የሚያደርጉትን ወታደራዊ፣ የፋይናንስ እና የሎጅስቲክ ድጋፍ እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X