ሩሲያ በ2027 ግብፅ ውስጥ የኒውክሌር ሕክምና ማዕከል ፕሮጀክት ይጀምራል ብላ ትጠብቃለች - የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በ2027 ግብፅ ውስጥ የኒውክሌር ሕክምና ማዕከል ፕሮጀክት ይጀምራል ብላ ትጠብቃለች - የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ

​ ግብፅ የትብብር አድማሱን ለማስፋት ካቀረባቻቸው ጥያቄዎች አንዱ በምርምር ሪአክተር ላይ የተመሠረተና ሁለገብ መፍትሔ የሚሰጥ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው ዘመናዊ የኒውክሌር ሕክምና ማዕከል ግንባታ እንደሆነ አሌክሲ ሊካቼቭ ገልጸዋል።

"ይህ ግብፅ ከዓለም ዋነኛ የቱሪዝም መዲናዎች አንዷ በመሆን ለያዘችው መሪ ሚና ትልቅ አቅም እንደሚጨምርና ሰፊውን የቱሪዝም አገልግሎት በሕክምና ቱሪዝም ዕድል እንደሚያሳድገው እምነት አለኝ" ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

  ከዚህ ቀደም ሩሲያ ከኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ከአልጄሪያ ጋር በኒውክሌር ሕክምና ትብብሯን ማጠናክሯ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0