ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ብሔራዊ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማዕቀፍ ቀረጸች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ብሔራዊ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማዕቀፍ ቀረጸች
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ብሔራዊ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማዕቀፍ ቀረጸች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.08.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ብሔራዊ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማዕቀፍ ቀረጸች

ማዕቀፉ የተዘጋጀው በሲዳማ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሐረሪ ክልሎች የተካሄዱ የሙከራ ፕሮጀክቶችን መሠረት በማድረግ ነው።

ግብርና ሚኒስቴር፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የክልል ቢሮዎች እና የመንግሥት እና የግል ማኅበራት በፕሮጀክት ቀረጻው ላይ እንደተሳተፉ ዓለም አቀፉ የውሃ አስተዳደር ኢንስቲትዩት ገልጿል።

የሙከራ ፕሮጀክቶቹ ትኩረት የነበሩ ጉዳዮች፦

የግል ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ፣

የታሪፍ መዋቅሮች፣

በአፈፃፀም ላይ የተመሠረቱ ውሎች፣

የአርሶ አደሮች የመክፈል ፍላጎት፣

ከአገልግሎቶች አስተማማኝነት ጋር የተያያዙ መረጃዎች።

የኢትዮጵያ የመስኖ ልማት አቅም ከ5.3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ቢገመትም እስካሁን የለማው 10% ያህሉ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0