የኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሕክምና ቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ውጥን
18:59 25.08.2026 (የተሻሻለ: 19:04 25.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሕክምና ቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ውጥን
ሀገሪቱ ይህን ግብ ለማሳካት የሥራ ዕቅድ አዘጋጅታ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ የኢትዮጵያ ጤና ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ግርማ አባቢ መግለጻቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ይህንን ግብ ለማሳካት መደረግ አለባቸው የተባሉ ጉዳዮች፦
▪ የጤና ተቋማት ደረጃን ማሻሻል፣ ግብዓት ማሟላትና ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት፣
▪ የዲጂታል ጤና እና የሰው ሠራሽ አስተውህሎት አሠራሮችን ማስፋፋት፣
▪ የሕክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት፣
▪ የገንዘብና የግብዓት እጥረትን በጋራ ለመፍታት የመንግሥትና የግል አጋርነትን ማሳደግ።
ዕቅዱ ዜጎች በውጭ ሀገራት ለሕክምና ከሚያወጡት ወጪ በመታደግ ሀገር ውስጥ ጥራት ያለው ሕክምና እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X