በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 290 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገነቡ
17:28 25.08.2026 (የተሻሻለ: 17:34 25.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ 290 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገነቡ
ባለፉት ሦስት ዓመታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ከማኅበረሰቡ በተሰበሰበ 4.8 ቢሊዮን ብር ከተገነቡት ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ የነባሮቹን ደረጃ የማሻሻልና የመጠገን ሥራ መከናወኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
በተሰበሰበው ሀብት ፦
▪ 290 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እና2 ሺህ 792 አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ለአገልግሎት በቅተዋል፣
▪ 10 ሺህ 092 የመማሪያ ክፍሎች ጥገና ተደርጎላቸዋል፣
▪ 73 ሺህ 863 አዳዲስ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮች ተገዝተው ተሰራጭተዋል፡፡
ይህ የመሠረተ ልማት ግንባታ ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን ጠቅሶ የመንግስት የመገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X