ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ስትራቴጂክ የብሪክስ ትብብር መስክ አድርጋ አቀረበች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ስትራቴጂክ የብሪክስ ትብብር መስክ አድርጋ አቀረበች

በህንድ ጃይፑር በተካሄደ የብሪክስ የቱሪዝም ሚኒስትሮች ስብሰባ የኢትዮጵያ ልዑክ የሀገሪቱን ባሕላዊ ቅርሶች እና ተፈጥሯዊ መስህቦች አስተዋውቋል።

ሀገሪቱ ለዘላቂ ቱሪዝም፣ ለዲጂታል ፈጠራ፣ ለሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና ለክህሎት ዕድገት ትኩረት መስጠቷንም ገልጿል።

ጠንካራ የብሪክስ ትብብር፦

ቱሪዝምን ለማስፋፋት፣

ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለመደገፍ፣

ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን፣

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ቁልፍ እንደሆነ ልዑኩ አጽንኦት ሰጥቷል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በማገናኘት በኩል ያለውን ሚና እና የአዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ማዕከል የመሆን አቅም አጉልቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0