ዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ሽልማት ለአፍሪካውያን ክፍት ሆነ

© telegram sputnik_ethiopiaዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ሽልማት ለአፍሪካውያን ክፍት ሆነ
ዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ሽልማት ለአፍሪካውያን ክፍት ሆነ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2026
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ሽልማት ለአፍሪካውያን ክፍት ሆነ

​በአኀጉሪቱ በፈጠራ፣ ማኅበራዊ እና ሰብዓዊ ተነሳሽነቶች ላይ የሚሳተፉ አፍሪካውያን እስከ ነሐሴ 25 ድረስ ማመልከት ይችላሉ።

ሽልማቱን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​🟠 10 ዋና ዋና ዘርፎች እና ልዩ ሽልማት፣

​🟠 በአጠቃላይ 205 ሺህ ዶላር የሽልማት ገንዘብ፣

​🟠 150 በሚበልጡ ባለሙያዎች እና በ50 የዳኞች አባላት ተገምግመው የሚመረጡ 100 ተወዳዳሪዎች፣

​🟠 በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከ1,000 በላይ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​እ.ኤ.አ በ2025 በተካሄደው ውድድር ከ27 ሀገራት ከ3,700 በላይ ማመልከቻዎች የቀረቡ ሲሆን ለተወዳዳሪዎች ድጋፍ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ድምፆች ተሰጥተዋል።

ከማመልከቻው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀጥሉ ቁልፍ የውድድሩ ምዕራፎች፦

​1⃣ ከጳጉሜ 2 - መስከረም 17 - የባለሙያዎች ግምገማ፣

2⃣ ከመስከረም 25 - ጥቅምት 3 - ክፍት ዓለም አቀፍ ድምፅ አሰጣጥ፣

3⃣ ከጥቅምት 3-5 — የፕሮጀክት ማብራሪያ ለዳኞች ማቅረብ፣

4⃣ ጥቅምት 5 - የአሸናፊዎች የሽልማት ሥነ-ሥርዓት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0