የሩሲያ ህፃናት ደም በዩክሬን እጅ ላይ ነው - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ህፃናት ደም በዩክሬን እጅ ላይ ነው - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የሩሲያ ህፃናት ደም በዩክሬን እጅ ላይ ነው - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ህፃናት ደም በዩክሬን እጅ ላይ ነው - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

​ "የዜለንስኪ አገዛዝ እና ራሱ ዜለንስኪ ህፃናትን የሚይዙት በዚህ መንገድ ነው" ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ ዩክሬን በሩሲያ ክራስኖዳር ከተማ በሚገኝ የግል ህፃናት ማዕከል ላይ ያካሄደችውን የድሮን ጥቃት አስመልክቶ አስተያየታቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጽ አስፍረዋል።

 

"ህፃናት ለእነሱ ምን ያህል ውድ እንደሆኑ የሚያወሩት ወሬ ሁሉ የኪየቭ አገዛዝ ከሕፃናት እስከ ተማሪዎች በሁሉም ዕድሜ በሚገኙ ህፃናት ላይ ከሚፈፅመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ጋር ሲታይ ፉርሽ ነው።"

 

ዛካሮቫ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ ሀገራት የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን "በኪየቭ አገዛዝ እጅ ላይ ያለውን የህፃናት ደም" ማየት ተስኗቸዋል ስሉም ከሰዋል።

በክራስኖዳር ጥቃት እድሜያቸው 13፣ 15 እና 16 የሆኑ ሦስት ህፃናት መገደላቸውን፣ ሌሎቹ ስድስቱ ደግሞ የፍንዳታ ፍንጣሪ ቁስል፣ የቃጠሎ እና ከፍተኛየጭንቅላት  ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ለማግኘት ሆስፒታል መግባታቸውን የህፃናት መብቶች ኮሚሽነር ማሪያ ሎቮቫ-ቤሎቫ ​ቀደም ሲል ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0