ሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች በደቡብ ሱዳን የወርቅ ማውጣት ሥራ ጀመሩ

© telegram sputnik_ethiopiaሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች በደቡብ ሱዳን የወርቅ ማውጣት ሥራ ጀመሩ
ሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች በደቡብ ሱዳን የወርቅ ማውጣት ሥራ ጀመሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2026
ሰብስክራይብ

ሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች በደቡብ ሱዳን የወርቅ ማውጣት ሥራ ጀመሩ

​ በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ኢኳቶሪያ እና ማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ክልሎች በሚገኙ ቦታዎች ሥራ መጀመሩን በጁባ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ኮስሞደሚያንስኪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

 

“ሩሲያ የኢነርጂ እና የነዳጅ ዘርፎችን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ከፍተኛ ልምድና እውቀት አላት” ብለዋል።

ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት ደቡብ ሱዳን የመሠረተ ልማት አውታሮቿን ማዘመን ያስፈልጋታል ሲሉ አምባሳደሩ አክለዋል።

አምባሳደሩ ሁለቱ ሀገራት በሚከተሉት ዘርፎች ሰፊ የትብብር ዕድል እንዳላቸው ጠቁመዋል፦

ማዕድን ማውጣት፣

ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ፣

ኢነርጂ፣

ኢንዱስትሪ እና አምራች ዘርፍ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0