እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የምድር ወረራዋን ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ነው?

© telegram sputnik_ethiopiaእስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የምድር ወረራዋን ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ነው?
እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የምድር ወረራዋን ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ነው? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.08.2026
ሰብስክራይብ

እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የምድር ወረራዋን ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ነው?

​ እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በአሊ አል-ታኸር ኮረብታዎች የምታካሂደው ተከታታይ እና ከፍተኛ ጥቃት፤ "የተወሰነ የምድር ዘመቻ ለመጀመር ወይም በድርድር ወቅት በሊባኖስ እና ሄዝቦላህ ላይ ጫና ለመፍጠር" የምታደርገውን ዝግጅት የሚያሳይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ሊባኖሳዊው ወታደራዊ ባለሙያ አሊ ኢዜዲን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባለሙያው የዝግጅት ምልክቶች ናቸው ያሏቸውን ነጥቦችም ጠቁመዋል፡-

​🟠 የእስራኤል ወታደራዊ ኃይሎች መሰባሰብ፣

​🟠 ጥቃቶቹ ከዳርቻ አካባቢዎች ወደ ጥልቅ ቦታዎች መሸጋገራቸው፣

​🟠 መጠነ ሰፊ የወታደራዊ ኢንጂነሪንግ ሥራዎች፣

​🟠 የአቅርቦት መስመሮችን ለማቋረጥ የሚደረጉ ሙከራዎች።

​በሌላ በኩል፤ በተራራማ እና በተመሸጉ ቦታዎች ላይ የሚደረግ ወታደራዊ ዘመቻ፤ እጅግ ፈታኝ በመሆኑ ስለ ረጅም ጊዜ የእስራኤል ወረራ ለመናገር ወቅቱ ላይሆን ይችላል ሲሉ ኢዜዲን አጽንኦት ሰጥተዋል።

​የቀድሞው የሊባኖስ ብሪጋዴር ጄኔራል አንቱዋን ምራድም፤ የእስራኤል ተከታታይ ጥቃቶች የሄዝቦላህን መከላከያ ለማዳከም፣ ምሽጎችንና ዋሻዎችን ለማፈራረስ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ የአቅርቦት መስመሮችን ለማቋረጥ የተቃጣ ሊሆን ሲሉ ሐሳቡን ተጋርተዋል።

አሊ አል-ታኸር ለእስራኤል ተነጥሎ የሚታይ ከፍታ ሳይሆን፤ የደቡብ ሊባኖስ የመከላከያ እና ጂኦግራፊያዊ ስርዓት አካል እንደሆነም ነው ጄነራሉ የገለጹት።

​ ሊባኖስ እና እስራኤል በአሜሪካ አሸማጋይነት ሰኔ 19 ቀን በዋሽንግተን የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ ደቡባዊ ሊባኖስ ደረጃ በደረጃ በሀገሪቱ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሚውል እና እስራኤል ለቃ በምትወጣባቸው አካባቢዎች ሄዝቦላህ ትጥቁን እንደሚፈታ ያስቀምጣል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0