በሩሲያ አሸማጋይነት ከ1,400 በላይ የማዕከላዊ አፍሪካ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ
15:50 24.08.2026 (የተሻሻለ: 15:54 24.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሩሲያ አሸማጋይነት ከ1,400 በላይ የማዕከላዊ አፍሪካ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ
እጃቸውን ከሰጡት ታጣቂዎች ውስጥ 932ቱ በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ውስጥ ተሳትፈዋል ሲሉ የዓለም የደህንነት መኮንኖች ሕብረትን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ፕሬዚዳንት አርካንጀ ቱዋዴራ እ.ኤ.አ በ2019 የታዩ አስተዳደራዊ መዘግየቶች እንዲቀረፉ በጠየቁት መሠረት፤ የሩሲያ አሠልጣኞች የ "3አር" እና "ዩፑሲ" ቡድኖችን ትጥቅ የማስፈታት ኃላፊነት መረከባቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ ገልጿል።
ሩሲያውያኑ አሠልጣኞች በተጨማሪም፦
ከሁሉም አዛዦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መስርተዋል፣
እ.ኤ.አ በ2019 የተዘረጉትን የቡድን አዛዦች የመገናኛ መስመሮች እንደገና ሥራ አስጀምረዋል፣
የሎጂስቲክ ድጋፍ እና ቀጥተኛ ቅንጅት ፈጥረዋል።
ℹ ሂደቱ እ.ኤ.አ በ2019 የካርቱም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እና በምዕራባውያን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቢሮክራሲያዊ አሠራር ምክንያት ዘግይቶ እንደነበር ድርጅቱ ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X