የጊቤ ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አነስተኛ ውሃ እንደያዘ ተገለጸ
14:55 24.08.2026 (የተሻሻለ: 15:04 24.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጊቤ ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አነስተኛ ውሃ እንደያዘ ተገለጸ
ግድቡ በምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ክረምቱን በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ የያዘው የውሃ መጠን ዝቅተኛ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪካ ኃይል አስታውቋል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሹብር ባልቻ፤ የአየር ንብረት ለውጡ በኃይል አቅርቦት ላይ ችግር እንዳይፈጥር በኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ በጣቢያ ተገኝተው የመስክ ምልከታ ሲያደርጉ አሳስበዋል።
ጊቤ ሦስት በዓመት እስከ 6 ሺህ 500 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ከፍተኛውን የኃይል ድርሻ ይይዛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X