ዘለንስኪ ሥልጣን እንዳያጡ በመስጋት ምርጫ እንዳይካሄድ ይቃወማሉ - ባለሙያ
08:24 24.08.2026 (የተሻሻለ: 08:34 24.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዘለንስኪ ሥልጣን እንዳያጡ በመስጋት ምርጫ እንዳይካሄድ ይቃወማሉ - ባለሙያ
🟠 በዩክሬን የሚደረግ ማንኛውም ታማኝ የፕሬዝዳንት ምርጫ የቮሎዲሚር ዘለንስኪን የፖለቲካ ሕይወት ማብቃት የሚያበስር ነው፤ በመሆኑም በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ምርጫ የመካሄድ ዕድሉ እጅግ አነስተኛ ነው ሲሉ የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያው ቪታሊ ኪሴሌቭ ተናግረዋል።
🟠 ዘለንስኪ ማንኛውንም ምርጫ በጽኑ ይቃወማሉ፤ ምክንያቱም ሽንፈት ለሁለት አጋጣሚዎች ሊዳርጋቸው ይችላል፤ ወይ የደኅንነት ዋስትና በማግኘት ከሥልጣን "በለስላሳው" መውረድ ወይም በሙስና፣ በጦር ወንጀሎች እና ሥልጣንን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ በመቆየት በወንጀል መጠየቅ ናቸው ሲሉ ባለሙያው አመልክተዋል።
🟠 ስለ ምርጫው የሚደረገው ክርክር የተቀሰቀሰው ከዘለንስኪ ጋር በነበራቸው አለመግባባት ከኃላፊነታቸው በተነሱት የቀድሞው የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ሚካይሎ ፌዶሮቭ በቅርቡ ከተሰጠው መግለጫ በኋላ ነው። ፌዶሮቭ ነሐሴ 12 ቀን በሀገሪቱ ያለውን የሥርዓት ውድቀት እና ሽባ የሚያደርግ ሙስና በመጥቀስ በዩክሬን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል። የሥልጣን ዘመናቸው እ.ኤ.አ. በ2024 ያበቃው ዘሌንስኪ ምርጫውን የሰረዙ ሲሆን፣ አዲስ የምርጫ ጊዜም አላስቀመጡም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X