ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል ብሔራዊ ፍኖተ-ካርታ ልታዘጋጅ ነው

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል ብሔራዊ ፍኖተ-ካርታ ልታዘጋጅ ነው

ፍኖተ-ካርታው በግብርና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት "ብሪጅ ፕላስ" ፕሮጀክት ትብብር እየተዘጋጀ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ብሔራዊ ፍኖተ-ካርታው የሚከተሉትን ተሞክሮዎች ለወተት ላም አርቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።

🟠 የቴክኖሎጂ፣

🟠 የገበያ ትስስር እና

🟠 በአቅም ግንባታ

"ብሪጅ ፕላስ" ፕሮጀክት ፕሮጀክት እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት የነጠላ ላም የቀን የወተት ምርትን በአማካይ በ3.8 ሊትር ማሳደግ ተችሏል። ይህን ስኬት አጠናክሮ ለማስቀጠልም በ5 ዓመታት የምርት ዘመን "ላም-ተኮር የምክር አገልግሎትን" ለ350 ሺህ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0