https://amh.sputniknews.africa/20260823/5011987.html
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
Sputnik አፍሪካ
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች ከጦርነቱ ከአንድ ዓመት በፊት ገደማ በ250 ሺህ ዶላር ወጪ የገነባችውን በራፋህ የሚገኘውን ጂም ካጣች በኋላ፣ የፍልስጤም... 23.08.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-08-23T18:24+0300
2026-08-23T18:24+0300
2026-08-23T18:34+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/08/17/5011834_0:0:1280:720_1920x0_80_0_0_385cd98e6b2c723246c9234367c5b9ae.jpg
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች ከጦርነቱ ከአንድ ዓመት በፊት ገደማ በ250 ሺህ ዶላር ወጪ የገነባችውን በራፋህ የሚገኘውን ጂም ካጣች በኋላ፣ የፍልስጤም የሰውነት ማጎልበት ፌዴሬሽን አባል የሆነችው ኢማን አል-ሙጋየር ተልዕኮዋን በተፈናቃይ ድንኳኖች ውስጥ ለመቀጠል ወስናለች።"ሁሉንም ነገር ካጣሁ በኋላ ‘እንዴት እንደገና መጀመር እችላለሁ?’ ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። ሥልጠናውን እዚሁ ድንኳን ውስጥ ለመጀመር ያኔ ነው ሐሳቡ የመጣልኝ" ስትል ለስፑትኒክ ተናግራለች። አል-ሙጋየር የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን የክብደት ማንሻዎችን የመግዛት አቅም እንደሌላቸው ተገነዘበች፤ በመቀጠልም በእያንዳንዱ ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የዕለት ተዕለት ቁሳቁሶችን በአሸዋ የተሞሉ ባዶ የምግብ ዘይት ቆርቆሮዎችን ለሥልጠና የሚሆኑ አማራጭ ክብደቶች አድርጎ የመጠቀም ሐሳብ አመጣች። ድንጋዮችና የሽምብራ ቆርቆሮዎችም ለዚሁ ዓላማ ያገለግላሉ።"ዓላማዬ ያን ያህል የአካል ብቃት ማጎልበት ሳይሆን የሥነ-ልቦና እፎይታ መስጠት ነው። አእምሯዊ ብርታት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው" ስትል አሠልጣኟ ደምድማለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
Sputnik አፍሪካ
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
2026-08-23T18:24+0300
true
PT1S
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/08/17/5011834_160:0:1120:720_1920x0_80_0_0_a9dcff456edff0f4f734af6ff972ca74.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
18:24 23.08.2026 (የተሻሻለ: 18:34 23.08.2026) የአካል ብቃት አሠልጣኟ በጋዛ የተፈናቃይ ድንኳን ውስጥ ሴቶችን ለማሠልጠን የእርዳታ ዕቃዎችን ወደ ክብደት ማንሻነት ለወጠች
ከጦርነቱ ከአንድ ዓመት በፊት ገደማ በ250 ሺህ ዶላር ወጪ የገነባችውን በራፋህ የሚገኘውን ጂም ካጣች በኋላ፣ የፍልስጤም የሰውነት ማጎልበት ፌዴሬሽን አባል የሆነችው ኢማን አል-ሙጋየር ተልዕኮዋን በተፈናቃይ ድንኳኖች ውስጥ ለመቀጠል ወስናለች።
"ሁሉንም ነገር ካጣሁ በኋላ ‘እንዴት እንደገና መጀመር እችላለሁ?’ ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። ሥልጠናውን እዚሁ ድንኳን ውስጥ ለመጀመር ያኔ ነው ሐሳቡ የመጣልኝ" ስትል ለስፑትኒክ ተናግራለች።
አል-ሙጋየር የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን የክብደት ማንሻዎችን የመግዛት አቅም እንደሌላቸው ተገነዘበች፤ በመቀጠልም በእያንዳንዱ ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የዕለት ተዕለት ቁሳቁሶችን በአሸዋ የተሞሉ ባዶ የምግብ ዘይት ቆርቆሮዎችን ለሥልጠና የሚሆኑ አማራጭ ክብደቶች አድርጎ የመጠቀም ሐሳብ አመጣች። ድንጋዮችና የሽምብራ ቆርቆሮዎችም ለዚሁ ዓላማ ያገለግላሉ።
"ዓላማዬ ያን ያህል የአካል ብቃት ማጎልበት ሳይሆን የሥነ-ልቦና እፎይታ መስጠት ነው። አእምሯዊ ብርታት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው" ስትል አሠልጣኟ ደምድማለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X