ለአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ታካሚዎች በባንክ ሂሳባቸው 1.5 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ሊኖራቸው ይገባል - ጤና ሚኒስቴር
ለአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ታካሚዎች በባንክ ሂሳባቸው 1.5 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ሊኖራቸው ይገባል - ጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስቴር ከሀገር ውጭ ለሚደረጉ የሕክምና ውክልናዎች አዲስ ጥብቅ መመሪያ ያወጣ ሲሆን የውጭ ሕክምና የሪፈራል ወረቀት መስጠት የሚችሉት አጠቃላይ የሪፈራል ወይም ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ሆስፒታሎች ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተፈርሞበታል ተብሎ በሀገር ውስጥ ሚዲያ የተዘገበው "ከሀገር ውጭ የሕክምና አገልግሎት የሪፈራል ሥርዓት አፈፃፀም" መመሪያ ምን አካቷል?
🟠 ለአጠቃላይ ሕክምና ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ታካሚዎች በባንክ ሂሳባቸው ቢያንስ 500 ሺህ ብር ተቀማጭ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
🟠 ለአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ ለሚጓዙ ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ሊኖራቸው ይገባል።
🟠 ለአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ የታካሚውና የለጋሹ ሕጋዊ ስምምነት እንዲሁም የሕክምና ባለሙያው ብቃት ማረጋገጫ መቅረብ አለበት።
🟠 ፈቃድ የሚሰጠው ሕክምናው በኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ከአቅም በላይ ሲሆን (የምርመራ መሣሪያ ወይም የልዩ ባለሙያ እጥረት፣ ረጅም የጥበቃ ጊዜ ወይም የናሙና ምርመራዎችን ወደ ውጭ መላክ የማይቻል ሲሆን) ወይም ለቀጣይ ክትትል ብቻ ይሆናል።
🟠 ውሳኔው ከ3 እስከ 5 አባላት ባሉት የሜዲካል ቦርድ መፅደቅ አለበት።
🟠 ቦርዱ ለታካሚው 1 ተንከባካቢ የሚፈቅድ ሲሆን፣ በልዩ ሁኔታዎች እስከ 2 ተንከባካቢዎችን ሊፈቅድ ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X