በአዲስ አበባ የሚከሰት ነገር አዲስ አበባ ብቻ አይቀርም - የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት
20:04 22.08.2026 (የተሻሻለ: 20:14 22.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የሚከሰት ነገር አዲስ አበባ ብቻ አይቀርም - የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት
የኢትዮጵያ የእርቅ ጥረትና የሚሰፍነው ሰላም የቀጣናውን ደህንነት እንደሚያጠናክር፣ የንግድ መስመሮችን እንደሚከፍት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን እንደሚያስገኝ ኡሁሩ ኬንያታ በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማጠቃለያ ሥነ-ስርዓት ላይ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ ሰላምን ስትመርጥ የንግድ መስመሮች ይከፈታሉ፣ ኢኮኖሚ ይረጋጋል፣ የጋራ ድንበሮቻችንም የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል፤ የአፍሪካ ልብ በጭንቅ ላይ እያለ የበለፀገች አህጉር ልትኖረን አትችልም" ብለዋል።
የአፍሪካ ሀገራት ለፖለቲካዊ እና ልማታዊ ፈተናዎቻቸው የውስጥ መፍትሔዎችን ሊከተሉ እንደሚገባ ጥሪ በማቅረብ፤ የአኅጉሪቱ መጻኢ ዕድል ከውጭ በሚጫኑ ሞዴሎች ሊወሰን እንደማይገባም ኡሁሩ አሳስበዋል።
"አፍሪካ ግጭቶችን ለመፍታት እና መልካም አስተዳደርን ለማጠናከር የሚያስችሉ የራሷ ባህላዊ የእርቅ ስርዓቶች፣ የሕግ ባለሙያዎች እና ባህላዊ ሀብቶች ያሏት አኅጉር ናት።"
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያን ክልሎች ከነጸጋዎቻቸው በወጉ በማቅረብ፤ በፓን-አፍሪካዊነት የተገለጠ በብዝኃነት ውስጥ ያለውን የሀገሪቱ ሕዝብ አንድነት አጉልተው ያቀረቡበት የ30 ደቂቃ ንግግር ታዳሚያንኑ አስደምሟል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X