በዩክሬን ላይ የሚሰነዘሩት የሩሲያ ጥቃቶች ውጤታማ እና ወቅታዊ ናቸው - ፑቲን

በዩክሬን ላይ የሚሰነዘሩት የሩሲያ ጥቃቶች ውጤታማ እና ወቅታዊ ናቸው - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዋና ዋና መግለጫዎች፦
በዩክሬን ኢላማዎች ላይ የሚሰነዘሩት የሩሲያ ጥቃቶች ግባቸውን እያሳኩ እና የፊት ለፊት የውጊያ እንቅስቃሴዎችን እየደገፉ ይገኛሉ።
ጥቃቶቹ የዩክሬን የመከላከያ-ኢንዱስትሪ ተቋማት መሣሪያዎቻቸውን የማዘመን አቅምን ያሰናክላሉ።
በውጊያ እንቅስቃሴዎች አፈጻጸም ላይ ቀጥተኛ እና በጎ ተፅዕኖ አላቸው።
ዩክሬን እና ዘዋሪዎቿ በሩሲያ ላይ ምንም ዓይነት የበላይነት አላገኙም፤ ወደፊትም አያገኙም።
የኪዬቭ አገዛዝ በሲቪል ኢላማዎች ላይ ጥቃት መክፈት ሲጀምር "የንብ ቀፎ መንጋን" ነካክቶ እንደሚቀሰቀስ ነው፤ አሁንም ምላሽ እየተቀበለ ይገኛል።
ፑቲን ዩክሬን እና ምዕራባውያን "ሩሲያን በ40 ቀናት ውስጥ ለማሸነፍ " ያደረጉትን ሙከራ እንደ ሌላ ተጨማሪ ቁማር አናንቀውታል።
ባላጋራዎች ሩሲያን ወደ ውድቀት ለማድረስ ለረጅም ጊዜ አልመዋል፤ ነገር ግን አይሳካላቸውም።
ሩሲያ በጠላት የሎጂስቲክስ ጥቃቶች ምክንያት በኪየቭ የሚገኙትን ጨምሮ በዩክሬን የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ላይ የምታካሂደውን ጥቃት አጠናክራለች፤ የሩሲያ የበቀል ምላሽም "ይበልጥ አሳማሚ እና አጥፊ" ነው።
የግብርናውን ዘርፍ ጨምሮ የዩክሬን ኢኮኖሚ "በግድ ነው እየተነፈሰ ያለው"።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X