የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከወሰዱት ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡት 12.8 በመቶ ያህሉ ናቸው - ትምህርት ሚኒስቴር
19:12 22.08.2026 (የተሻሻለ: 19:14 22.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከወሰዱት ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡት 12.8 በመቶ ያህሉ ናቸው - ትምህርት ሚኒስቴር
የዘንድሮውን ፈተና ከወሰዱት 550,210 ተማሪዎች ውስጥ 70,544ቱ ግማሽና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የሚኒስተሩ ቁልፍ መግለጫዎች፦
በተፈጥሮ ሳይንስ 591.6 ፤ በማኅበራዊ ሳይንስ 576.25 ከፍተኛ ውጤቶች ሆነው ተመዝግበዋል።
563,960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550,210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
88 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።
ፈተናው በኮምፒውተርና በወረቀት ታግዞ ተሰጥቷል።
የተማሪዎች ውጤት ሰኞ አመሻሽ አልያም ማክሰኞ ይፋ ይደረጋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X