ሩሲያ ከምዕራባውያን አገራት በተለየ መልኩ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የኒውክሌር አጋርነትን ታቀርባለች - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ ከምዕራባውያን አገራት በተለየ መልኩ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የኒውክሌር አጋርነትን ታቀርባለች - ባለሙያ
ሩሲያ ከምዕራባውያን አገራት በተለየ መልኩ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የኒውክሌር አጋርነትን ታቀርባለች - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.08.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ከምዕራባውያን አገራት በተለየ መልኩ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የኒውክሌር አጋርነትን ታቀርባለች - ባለሙያ

“ምዕራባውያን የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማካካስ እና በኒውክሌር ዑደት እንዲሁም በዩራኒየም ማበልጸግ ላይ ራሳቸውን ለመቻል ይፈልጋሉ። ለዚህም ሲሉ ከሩሲያ የሚገቡ የበለጸጉ ዩራኒየሞች ላይ ገደብ እየጣሉ ነው” ሲሉ የኃይል ዘርፍ ባለሙያ እና የግብፅ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች ባለሥልጣን የቀድሞ ምክትል ሊቀመንበር አሊ አብደል ናቢ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሩሲያ በእፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ ሰፊ የኒውክሌር አጋርነት እድሎችን የምታቀርብ ሲሆን፣ ከምዕራባውያን የኑክሌር ፕሮጀክቶች በግልጽ የተለየ ሞዴል ታቀርባለች ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

የሮሳቶም የተገነቡ ማመንጫዎች በተለያዩ ክልሎች ውስጥ እንደ "ለሰላማዊ አገልግሎት" መሳሪያ በመሆን ከመገልገላቸውም በላይ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ ያለውን መረጋጋት የሚያጠናክሩ በመሆናቸው፣ በሩሲያ የኒውክሌር ኢንዱስትሪ ላይ ያለው እምነት እጅግ በጣም ጠንካራ እንደሆነ ይ ቀጥላል።

“የሩሲያ ንግግር ከልማት ማስታወቂያዎች አልፎ ጂኦፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ደህንነታዊ ይዘት ያለው ስትራቴጂካዊ መልእክት ሆኗል፤ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ኃይሎችም ትኩረት እየሰጡት ነው” ሲሉ አጠናቅቀዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል ባደረጉት ንግግር የላቁ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እቅድ ሲያስተዋውቁ፣ ሩሲያን በኒውክሌር ኃይል ዘርፍ የዓለም መሪ እና ሙሉ የቴክኖሎጂ ሰንሰለት እውቀት ያላት ብቸኛ ሀገር አድርገው አቅርበዋታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0