የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ የጭነት መጠን 17.57 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደረሰ
15:24 22.08.2026 (የተሻሻለ: 15:34 22.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ የጭነት መጠን 17.57 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደረሰ
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከ17.57 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የገቢና የወጪ ንግድ ጭነት ስታጓጉዝ ቡና 440 ሺህ ሜትሪክ ቶን (26.79%) በመያዝ በወጪ ንግድ ቀዳሚውን ድርሻ መያዙን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
የጭነት ዓይነት፦15.93 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የገቢ (ነዳጅ፣ ጄኔራል ካርጎና ደረቅ ብትን)፣ 1.64 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶኑ የወጪ ንግድ ጭነት ነው።
የማጓጓዣ ዘዴ፦ 80.15% በየብስ፣ 18.92% በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር፣ እና 0.94% በአየር ካርጎ ተስተናግዷል።
የኮሪደር ድርሻ፦ የጂቡቲ ወደብ 96.71% (15.34 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን)፣ በበርበራ (2.74%)፣ ታጁራ (1.23%) እና ሞምባሳ-ሞያሌ (0.56%) ኮሪደሮች ተስተናግዷል።
የወጪ ንግድ፦ 74.78% ኮንቴይነሮች ሀገር ውስጥ በመታሸጋቸው 12.08 ሚሊዮን ዶላር ድኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X