ኢትዮጵያ የእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳን 76 በመቶ ማድረሷን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳን 76 በመቶ ማድረሷን አስታወቀች

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ አዲስ አበባ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ጉባዔ ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ይፋ ባደረጉበት ወቅት በእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

የሚኒስትሯ መግለጫ ቁልፍ ነጥቦች፦

🟠 የእናቶች ሞት ምጣኔ ቅነሳ ከነበረበት 6 በመቶ ወደ 76 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ ከ100 ሺህ በሕይወት ከሚወለዱ ሕፃናት መካከል ይሞቱ የነበሩት ቁጥር ከ871 ወደ 141 ዝቅ ብሏል።

🟠 በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ የ47 የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በአኅጉራዊ የጤና ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ይመክራሉ።

ኢትዮጵያ 5 የጤና ጉዳዮችን ቀዳሚ አጀንዳ አድርጋ በጉባኤው የምጻተፍ ሲሆን፤ እነሱም፦

ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ግንባታ፣

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ፣

ዲጂታል ጤና፣

የጤና ባለሙያዎች እና

የጤና መሠረተ ልማት ዕድገት፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር መሐመድ ጃናቢ በበኩላቸው፣ ጉባዔው የ1.5 ቢሊዮን አፍሪካውያንን የጤና ዕጣ-ፋንታ የሚወስን መሆኑን ጠቅሰው፣ አኅጉሪቱ በሽታዎችን የመከላከል አቅሟን ለማሳደግ በራሷ የምትተማመንበት ደፋር እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0