"ኢትዮጵያ የዓባይ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አትጠይቅም" - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia"ኢትዮጵያ የዓባይ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አትጠይቅም" - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር
ኢትዮጵያ የዓባይ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አትጠይቅም - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.08.2026
ሰብስክራይብ

"ኢትዮጵያ የዓባይ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አትጠይቅም" - የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር

የዓባይ ወንዝ አዲሱ ውጥረት

የሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ ንግግር የተደመጠው፣ የግብጽ የውኃ እና የመስኖና ሀብት ሚኒስትር ሃኒ ሴዊላም ከቀናት በፊት ለመገኛኛ ብዙኃን በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ኢትዮጵያ አዳዲስ ግድቦችን የመገንባት እቅድ እንዳላት የሚታወቅ መሆኑን ጠቅሰው የግብጽ መንግሥት ይህ እንዲሆን እንደማይፈቅድ ከዛቱ በኋላ ነው፡፡

ያልተረጋገጠው ዕቅድ

የአዳዲስ ሦስት ግድቦች ግንባት ጉዳይ አስመልክቶ በኢትዮጵያ በኩል የቀረበ ይፋዊ ዕቅድ ባይኖርም፤ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ተከትሎ በግብጽ ባለሥልጣናት በኩል ተደጋጋሚ ዛቻዎች ተሰምተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት አቋም

የኢትዮጵያ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) "ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር ናት፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን የገነባነው ያለማንም ፈቃድ ነው፤ በሌሎች የወንዝ ተፋሰሶች ላይም ማልማት ሲያስፈልገን የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም" በማለት የሀገሪቱን ጽኑ አቋም በድጋሚ አስረግጠዋል።

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በበኩላቸው፣ “ግብጽ በናይል ወንዝ ላይ ተጨማሪ ግድቦች እንዲገነቡ አትፈቅድም።” ያሉ ሲሆን ሀገራቸው “ጥቅሟንና የውኃ ደህንነቷን የመጠበቅ ሕጋዊ መብት አላት።” ሲሉ ረቡዕ ዕለት ለሳዑዲ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከሀገር ውስጥ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ወቅት ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦

🟠 የሕዳሴው ግድብ ዓላማ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ብቻ ነው፡፡

ከግድቡ የሚመነጨው ኃይል ለኬንያ፣ ጂቡቲ እና ሱዳን እየቀረበ እንደሚገኝ፣ እንዲሁም ለሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ለማቅረብ እየተሠራ ነው፡፡

🟠 ግድቡን ከታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ የማስተዳደር ጥያቄን "በኢትዮጵያውያን ጥረት የተገነባንና የሀገር ኩራት የሆነን ፕሮጀክት ሲቃወም የነበረ አካል መጥቶ በጋራ እንምራው ማለቱ ፈጽሞ የማይታሰብና የማይቻል ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

🟠 ኢትዮጵያ የታችኞቹን የተፋሰስ ሀገራት ስጋት ለመቀነስ ስትል ከሕዳሴው ግድብ በታች የሚገኘውን ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ለመስኖ የሚሆን መሬት ሳታለማ ቆይታለች።

🟠 የታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴ ለማገድ ከመሞከር ይልቅ በውይይትና በትብብር መሥራት አለባቸው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0