ቸቡራሽካ በየካተሪንበርግ ለሚካሄደው የወጣቶች ፌስቲቫል ወካይ "ማስኮት" ሆነ

ሰብስክራይብ

ቸቡራሽካ በየካተሪንበርግ ለሚካሄደው የወጣቶች ፌስቲቫል ወካይ "ማስኮት" ሆነ

"ይህ ወዳጅነትን የተላበሰ ትንሹ ፍጡር ተሳታፊዎች ከሁሉም የዓለም ማዕዘናት አዳዲስ ወዳጆችንና የሚያውቋቸውን ሰዎች እንዲፈልጉ ያነሳሳል" ሲል መመረጡ በተበሰረበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተመላክቷል።

ቸቡራሽካ ማን ነው?

ትላልቅ ጆሮዎች ያሉት ይህ ገጸ-ባህሪ እ.ኤ.አ በ1966 በጸሐፊው ኤድዋርድ ኡስፔንስኪ የተፈጠረ ሲሆን፣ በ1969 እ.ኤ.አ በተከታታይ የሶቪዬት ካርቱኖች አማካኝነት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።

የመነሻ አመጣጡ ከአፍሪካ እንደሆነ ይነገራል።

ቸቡራሽካ ወደ ሶቪዬት ከተማ የደረሰው ከሩቅ ሀገር በመጣ የብርቱካን ሣጥን ውስጥ ሆኖ ሲሆን ይህም ሶቪዬት ሕብረት ከሞሮኮ የሲትረስ ፍራፍሬዎችን ታስገባ የነበረበትን ታሪክ የሚያስታውስ ነው።

ዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ከመስከረም 1 እስከ 7 በሚካሄደው መድረክ ከ190 ሀገራት የተወጣጡ 10,000 ተሳታፊዎችን የሚያገናኝ ይሆናል። ለዝግጅቱም ሐውልቶች እና ለስላሳ የጨርቅ አሻንጉሊቶች ለእይታ ይቀርባሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0