ኢትዮጵያ የኬንያ ኢ-መደበኛ ወጪ ንግድ 54 በመቶ መዳረሻ መሆኗ ተመላከተ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የኬንያ ኢ-መደበኛ ወጪ ንግድ 54 በመቶ መዳረሻ መሆኗ ተመላከተ

 

የኬንያ ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ ሀገሪቱ ወደ ጎረቤቶቿ ከምትልከው ኢ-መደበኛ (የድንበር/የኮንትሮባንድ) ወጪ ንግድ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ይዘዋል።

 

የሪፖርቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

🟠 እ.ኤ.አ በሰኔ 2025 በተካሄደው ጥናት መሠረት፣ ኢትዮጵያ የኬንያን ኢ-መደበኛ የወጪ ንግድ የጠቅላላውን 54 በመቶ (67 ሚሊዮን ሺሊንግ) ይዛለች። ኡጋንዳ በ29.1 በመቶ ትከተላለች።

 

🟠 ወደ ኢትዮጵያ ለሚላኩ የኬንያ ኢ-መደበኛ ምርቶች ሞያሌ ዋነኛው የድንበር መውጫ መስመር ሆኖ ተመዝግቧል።

 

🟠ምግብ ነክ ምርቶች፣ የቁም እንስሣት፣ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎችና ተያያዥ ምርቶች በድንበር አካባቢ በብዛት የሚንቀሳቀሱ የንግድ ዓይነቶች ናቸው።

 

🟠በድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች ዘንድ ከ40 በመቶ በላይ አገልግሎት ላይ የዋለው ዋነኛው የትራንስፖርት አማራጭ ሞተርሳይክል መሆኑ ተጠቅሷል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘው ቪዲዮ የሞያሌን ከተማ እንቅስቃሴ ያሳያል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0