ሱዳን ከአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የከዱ ተዋጊዎችን ወደ ብሔራዊ ጦር የመቀላቀል የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቀቀች

ሰብስክራይብ

ሱዳን ከአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የከዱ ተዋጊዎችን ወደ ብሔራዊ ጦር የመቀላቀል የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቀቀች

ይህ የመቀላቀል ሂደት የተከናወነው በዳርፉር፣ በኮርዶፋን እና በሰሜን ግዛት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጃቸውን የሰጡ ተዋጊዎችን ተከተሎ ሲሆን፣ በቅርቡም ከ300 በላይ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተዋጊዎችን የያዘ አንድ የጦር ክፍል እጁን መስጠቱን ጦሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ሂደቱን የሚከታተለውን ኮሚቴ በሚመሩት በብርጋዴር ጄኔራል ኢሳቅ ሳዕድ ኦስማን ገለጻ መሠረት፣ የሚከተሉት ሂደቶች ተከናውነዋል፡፡

🟠 አስተዳደራዊ ማስተካከያዎችን ማድረግ፤

🟠 የደህንነት እና የመረጃ ማጣሪያዎችን ማካሄድ፤

🟠 ወደ ኦፕሬሽናል የጦር ክፍሎች መመደብ።

ይህ እርምጃ የጦሩ አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ግጭቱ በሚያዝያ 2023 ከተቀሰቀሰ ወዲህ ያቀረቡት የሰላም ጥሪ አካል ነው።

ኦስማን አክለውም፣ "የከዱት ተዋጊዎች ከሀገራዊው የጦር ኃይል ጎን በመሰለፋቸው እናደንቃቸዋለን" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0