የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናት በካሜሩን ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን ገዳይ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዘጉ - መገናኛ ብዙኃን

ሰብስክራይብ

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናት በካሜሩን ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን ገዳይ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዘጉ - መገናኛ ብዙኃን

ባለሥልጣናት ማክሰኞ ዕለት ቢያንስ የ49 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ከባድ የጉድጓድ መደርመስ ተከተሎ በዛምቦዬ የሚገኝ ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ሥራ በአስቸኳይ እንዲቆም ማዘዛቸውን፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የማዕድን ሚኒስትር ሩፊን ቤናም ቤልቱንጉን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሕይወታቸው ማለፉ ከተረጋገጡት መካከል 35 የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዜጎች፣ 12 ካሜሩናውያን እና 2 ቻዳውያን እንደሚገኙበት ሚኒስትሩ መግለፃቸው ተነግሯል።

ሆኖም ነፍስ የማዳን ጥረቱ ቀጣይ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊጨመር እንደሚችል የአካባቢው ባለሥልጣናት መስጋታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0