ሀገራዊ ምክክር፦ በአዲስ አበባ የባለቤትነት እና ሕጋዊ ማዕቀፍ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ የውሳኔ ሀሳብ የሚያዘጋጅ አዲስ ኮሚቴ ተዋቀረ

ሰብስክራይብ

ሀገራዊ ምክክር፦ በአዲስ አበባ የባለቤትነት እና ሕጋዊ ማዕቀፍ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ የውሳኔ ሀሳብ የሚያዘጋጅ አዲስ ኮሚቴ ተዋቀረ

 

በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተቋቋመው ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ላይ አስማሚ የመጨረሻ የውሳኔ ሐሳብ በማዘጋጀት ለጉባኤው እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

አቀራራቢ ኮሚቴው የቀረቡትን ቅሬታዎች መርምሮ የደረሰበትን ውጤት በዛሬው ዕለት (አርብ) ለተመካካሪዎች እንዲያቀርብ መወሰኑንም የጉባኤው ተሳታፊዎችን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

 

የጉዳዩ ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

🟠 የአለመግባባቱ መነሻ፦ የኮሚሽኑ የ120 አባላት አዘጋጅ ቡድን "አዲስ አበባ የፌደራል መንግሥቱ መቀመጫ ሆና ራሷን በራሷ የምታስተዳድር ከተማ ናት" የሚል ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡን ተከተሎ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ቅሬታ በማስገባታቸው ነው።

 

🟠 የቀረበው ቅሬታ፦ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች 'አዲስ አበባ የክልሉ ዋና መቀመጫ መሆኗ በሕገ-መንግሥቱ እንዲደነገግ'፣ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ በግልጽ ሊካተት ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

 

🟠 የአዲሱ ኮሚቴ ስብጥር፦ አዲሱ ኮሚቴ ከ12ቱ ክልሎች፣ከትግራይ ክልል ተወካዮች፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከምሁራን የተወጣጡ አባላትን ያካተተ ነው።

  

በዚህ ውዝግብ ምክንያት ለ4 ሺህ ተሳታፊዎች በይፋ ቀርቦ ትናንት እንደሚፀድቅ ሲጠበቅ የነበረው የሀገራዊ ምክክር መድረኩ ምክረ ሐሳብ ለተጨማሪ ሁለት ቀናት እንዲራዘም ተደርጓል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0