ለተመድ ዋና ጸሐፊነት ዕጩ ተወዳዳሪ ኡጋንዳዊ ዲፕሎማት አስቸኳይ ማሻሻያዎችን እና የግጭት አፈታትን ቅድሚያ እንደሚሰጡ ገለፁ
20:24 20.08.2026 (የተሻሻለ: 20:34 20.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለተመድ ዋና ጸሐፊነት ዕጩ ተወዳዳሪ ኡጋንዳዊ ዲፕሎማት አስቸኳይ ማሻሻያዎችን እና የግጭት አፈታትን ቅድሚያ እንደሚሰጡ ገለፁ
ተቋሙን ከገባበት ቀውስ ለማዳን እና ዓለም አቀፍ ልዩነቶችን ለማጥበብ የሚያስችለውን የሞራል ልዕልና ለመመለስ አስቸኳይ ማሻሻያዎችን ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ኡጋንዳዊው ዲፕሎማት እና የቀጣዩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊነት ቦታን ለመያዝ የሚወዳደሩት ኦላራ ኦቱኑ ገልጸዋል።
በዩክሬን፣ በጋዛ፣ በአፍሪካ ታላላቅ ሐይቆች ቀጣና እና በኢራን የሚገኙ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን መፍታት የቀጣዩ የተመድ መሪ ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
"ጠል ባለበት ፍቅርን፣ በደል ባለበት ይቅርታን፣ መጠራጠር ባለበት እምነትን፣ ተስፋ መቁረጥ ባለበት ተስፋን፣ ጨለማ ባለበት ብርሃንን፣ ኀዘን ባለበት ደስታን እዘራ ዘንድ እርዳኝ" ሲሉ ዲፕሎማቱ የቅዱስ ፍራንሲስን ጸሎት በመጥቀስ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ℹ የ75 ዓመቱ ኡጋንዳዊው ዲፕሎማት ኦላራ ኦቱኑ ቀደም ሲል የተመድ ንዑስ ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል። እሳቸው የወቅቱን የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ለመተካት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል አንዱ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X