የሩሲያ የኒውክሌር ኢንዱስትሪ 81ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ፤ ሮሳቶም አዳዲስ ግቦችን እና ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደረገ
19:24 20.08.2026 (የተሻሻለ: 19:34 20.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የኒውክሌር ኢንዱስትሪ 81ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ፤ ሮሳቶም አዳዲስ ግቦችን እና ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አደረገ
ሩሲያ በስድስት ሀገራት ተጨማሪ 17 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ክፍሎችን ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሷን የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሌክሴይ ሊካቼቭ ዛሬ ሐሙስ የኒውክሌር ኤነርጂ ልማት ስብሰባ ላይ ገልጸዋል።
የሊካቼቭ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
▪ ሮሳቶም በአሁኑ ወቅት ከ15 ሀገራት ጋር በአዳዲስ የኒውክሌር ኃይል ፕሮጀክቶች ላይ ድርድር በማድረግ ላይ ይገኛል።
▪ ቬትናም የቅርብ ጊዜ ማሳያ ስትሆን፣ ሩሲያ እና ቬትናም በቅርቡ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ላይ የመንግሥታት ደረጃ ስምምነት ተፈራርመዋል።
▪ ሩሲያ ዩራኒየምን ይበልጥ በብቃት ለመጠቀም እና የኒውክሌር ዝቃጭን ለመቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ የኒውክሌር ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ላይ ትገኛለች።
▪ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች አዲስ የኒውክሌር ኃይል ትውልድ ለማልማት እና በዓለም አቀፉ ኢንዱስትሪ ውስጥ የያዘችውን ቦታ ለማጠናከር ሩሲያ ካወጣቻቸው እቅዶች አካል ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X