የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ 40 ትሪሊዮን ዶላር በማለፍ አዲስ ታሪካዊ ሪከርድ አስመዘገበ

የአሜሪካ ብሔራዊ ዕዳ 40 ትሪሊዮን ዶላር በማለፍ አዲስ ታሪካዊ ሪከርድ አስመዘገበ
ከጥቂት ዓመታት በፊት ሊታሰብ የማይችል የነበረው የብድር ፍጥነት፣ የሀገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ አዲስ ክብረ-ወሰን ያስመዘገበ ሲሆን 39 ትሪሊዮን ዶላር በደረሰ በ5 ወራት ጊዜ ውስጥ ዕዳው በሌላ 1 ትሪሊዮን አድጓል።
በዚህ የበጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 9 ወራት ለወለድ ክፍያ ብቻ 827 ቢሊዮን ዶላር የወጣ ሲሆን፣ ይህም አሜሪካ ለመከላከያ ዘርፍ ከምታወጣው አጠቃላይ ወጪ በልጧል።
አሜሪካ በየቀኑ ለወለድ ብቻ በግምት 30 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የምታወጣ ሲሆን፣ የኮንግረስ የበጀት ጽሕፈት ቤት ሙሉ ዓመታዊ የወለድ ወጪው ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ገምቷል።
በ2030ዎቹ ደግሞ የወለድ ክፍያው ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ሊደርስ የሚችል ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላው የአሜሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ ወደ 5 በመቶ የሚጠጋውን ይይዛል።
በአሁኑ ጊዜ ዕዳው ከአጠቃላይ የአሚሪካ ኢኮኖሚ መጠን 122 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ደግሞ የጉዞው አቅጣጫ ዘላቂነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ አስጠንቅቋል።
የፒተር ጂ. ፒተርሰን ፋውንዴሽን አሜሪካ በስድስት ዓመታት ውስጥ ዕዳዋ 50 ትሪሊዮን ዶላር ልትደርስ ትችላለች ሲል ሲያስጠነቅቅ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በበኩሉ የሀገሪቱ ዕዳ እስከ 2029 ድረስ 50 ትሪሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ገምቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X