ኢትዮጵያ የከተማ ፕላን እና የቤቶች ልማት ልምዷን ለናሚቢያ አካፈለች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የከተማ ፕላን እና የቤቶች ልማት ልምዷን ለናሚቢያ አካፈለች

በናሚቢያ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስትር ሳንኳዋሳ ጀምስ የተመራ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ በከተሜነት፣ በከተማ የተቀናጀ ፕላን እና በቤቶች ልማት ዘርፍ ልምድ ልውውጥ አድርጓል።

ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ውይይት፦

🟠 ኢትዮጵያ በከተማ ፕላን፣ በተመጣጣኝ የቤቶች ልማት እንዲሁም በከተማ ውበትና ጽዳት ያመጣቻቸውን ተስፋ ሰጪ ተሞክሮዎች ለልዑካን ቡድኑ አጋርታለች።

🟠 የናሚቢያ ልዑክ በኢትዮጵያ በከተማ ልማትና ውበት ዘርፍ የታዩ ለውጦችን አድንቋል፤ ተሞክሮውንም በሀገራቸው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ይህ የልምድ ልውውጥ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ከማጠናከሩ ባሻገር በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች ዘርፎች የሚደረጉ የጋራ የትብብር ስራዎችን የሚያፋጥን መሆኑ ተመላክቷል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0