የሩሲያ ሚሳኤሎች ትናንት ማታ በኪዬቭ የትኞቹን ቦታዎች መቱ?

የሩሲያ ሚሳኤሎች ትናንት ማታ በኪዬቭ የትኞቹን ቦታዎች መቱ?
የሩሲያ ኃይሎች ሌሊቱን በኪዬቭ እና በዙሪያዋ ባሉ ወታደራዊ ፋብሪካዎች፣ የሎጂስቲክስ ማዕከላት እና የጦር መሣሪያ ዴፖዎች ላይ ያነጣጠሩ እና የረጅም ርቀት ድሮኖችን በመጠቀም ጥቃት ማድረሳቸውን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በዩክሬን ዋና ከተማ የተመቱት ኢላማዎች፦
ፋየር ፖይንት ኤልኤልሲ፦ የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ጥቃት አድራሽ ድሮኖች አካላትን የሚያመርት፣ እንዲሁም ለ"ፍላሚንጎ" ክሩዝ ሚሳኤሎች መገፋፊያዎችን የሚገጥም ተቋም፤
የዩክርስፔትሲስተም የመጋዘን ግቢ፦ የድሮን ክፍሎችን የሚያመርት፣ እንዲሁም ቋሚ ክንፍ ያላቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ሙሉ በሙሉ የሚገጥም እና የሚያከማች፤
የአንቶኖቭ የአውሮፕላን ፋብሪካ፦ ከመንገደኛ አውሮፕላኖች ምርት ጎን ለጎን የረጅም ርቀት አን-196 «ሊዩቲ» ድሮን የሚገነባበት፤
የጦር መሣሪያ ማከማቻ ዴፖ፦ ኤም-900 ቴርሞባሪክ ቦምቦች፣ የታንክ መቃወሚያ ፈንጂዎች እና ለባባ ያጋ ድሮኖች የሚያገለግሉ ጥይቶች የተከማቹበት።
ከከተማዋ ውጭ በኪዬቭ ክልል፦
የማርቱሶቭካ የሎጂስቲክስ ማዕከል፦ የድሮን ቁሳቁሶችን፣ ሮቦቲክስ እና የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ መሣሪያዎችን ጨምሮ ለሁለገብ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ለማከማቸት እና ለማሰራጨት የሚያገለግል ዋና ማዕከል፤
በብሮቫሪ የሚገኝ የነዳጅ ዴፖ፦ ለዩክሬን ኃይሎች የተዘጋጀ እስከ 8,000 ኩቢክ ሜትር ነዳጅ የያዘ።
ነሐሴ 13 አመሻሽ ላይም በጥቁር ባህር በሚገኙት በቼርኖሞርስክ እና በዩዥኒ የወደብ አካባቢዎች ባሉ ወታደራዊ የአቅርቦት መጋዘኖች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X