ሩሲያ በተሻሻሉ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች የግንባር መከላከያ ሥርዓቷን እንዳጠናከረች ሮስቴክ አስታወቀ
ሩሲያ በተሻሻሉ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች የግንባር መከላከያ ሥርዓቷን እንዳጠናከረች ሮስቴክ አስታወቀ
ሩሲያ የጦር ሜዳ መከላከያዋን በአዲስ የፓንትሲር-ኤስ ተንቀሳቃሽ የውጊያ ተሽከርካሪዎች እና በቋሚ የፓንትሲር-ከምድር-ወደ-አየር ተኳሽ የሚሳዔል ሥርዓት አጠናክራለች።
በመንግሥታዊው ሮስቴክ ኮርፖሬሽን የቀረቡት እነዚህ ወታደራዊ መሣሪያዎች፤ ሁሉንም ጥብቅ ፍተሻዎች አጠናቀው በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣናው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የላቁ የአየር መከላከያ ሥርዓቶቹ ዋና ዋና ባህሪያት፡-
🟠 ከፍተኛ የተኩስ አቅም፦ እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከሉት ሚሳዔል ማስወንጨፊያ ሳጥኖች እስከ 48 ሚሳዔሎች መያዝ የሚችሉ ሲሆን መደበኛ የመሬት-ወደ-አየር ሚሳዔሎችን፣ ከድምፅ የሚፈጥኑ ተወንጫፊዎችን እና የአጭር ርቀት አጨናጋፊ ሚሳዔሎችን መተኮስ ይችላሉ።
🟠 የ24 ሰዓት ሙሉ ጥበቃ፦ ሙሉ 24 ሰዓት መሥራት የሚችሉት ፓንትሲሮች፤ ከድሮን እስከ ባሊስቲክ እና ክሩዝ ሚሳዔሎችን በማክሸፍ፤ ሠራዊት እና የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ይከላከላሉ።
🟠 ጸረ-መንጋ ድሮን ቴክኖሎጂ፦ "የፓንትሲር-ከምድር-ወደ-አየር ተኳሽ የሚሳኤል ሥርዓት" ዓይነት፤ በተለየ ሁኔታ በመንጋ የሚሰነዘሩ የድሮን ጥቃቶችን ለመመከት የተሠራ ሲሆን በውጊያዎች ላይ ውጤታማነቱን እያስመሰከረ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X