የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በካርታ ዝግጅት ዙሪያ ትብብር ፈጠረ
16:47 19.08.2026 (የተሻሻለ: 16:54 19.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በካርታ ዝግጅት ዙሪያ ትብብር ፈጠረ
ተቋሙ ከሩሲያ ግዙፍ የዲጂታል ካርታ መፈለጊያ እና መምሪያ ኩባንያ 2ጂአይኤስ እና ስበርባንክ ተወካዮች ጋር በላቁ የጂኦስፓሻል መሣሪያዎች አጠቃቀም ዙሪያ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።
የውይይቱ ውጤት፦ 2ጂአይኤስ በኢትዮጵያ ተመረጠ ቦታ ማሳያ ካርታ ያዘጋጃል።
ለምን? መሣሪያዎቹ እና የአሠራር ሂደቶቹ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የካርታ ዝግጅት ሂደት ላይ እንዴት ሊተገበሩ እንደሚችሉ በተግባር ለመፈተሽ እና ለማሳየት።
ስምምነቱ በኢንስቲትዩቱ እና በሩሲያ አጋሮቹ መካከል ለቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ለአቅም ግንባታ እና ለረጅም ጊዜ ትብብር መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
ስበርባንክ በ2ጂአይኤስ ኢንቨስተር እና የምርቶቹ ተጠቃሚ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X