በኖርድ ስትሪም ጥቃት የተጠረጠረው ሁለተኛ ዩክሬናዊ ክሮኤሺያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ

© telegram sputnik_ethiopiaበኖርድ ስትሪም ጥቃት የተጠረጠረው ሁለተኛ ዩክሬናዊ ክሮኤሺያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በኖርድ ስትሪም ጥቃት የተጠረጠረው ሁለተኛ ዩክሬናዊ ክሮኤሺያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.08.2026
ሰብስክራይብ

በኖርድ ስትሪም ጥቃት የተጠረጠረው ሁለተኛ ዩክሬናዊ ክሮኤሺያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የጀርመን ፌደራል ዐቃቤ ሕግ እ.ኤ.አ 2022 በኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧዎች ላይ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ሁለተኛውን ዩክሬናዊ በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታውቋል።

ቭላዲሚር ዜድ በመባል የሚታወቀው ይህ ተጠርጣሪ፤ የጀርመን ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወርሃ ሰኔ 2024 ባወጣው የአውሮፓ የእስር ማዘዣ መሠረት ዛሬ በክሮኤሺያ የባሕር ዳርቻ ከተማ ፑላ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ግለሰቡ በመስከረም ወር 2022 በጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧዎቹ ላይ ፈንጂ ካጠመዱት ጠላቂ  ዋናተኞች አንዱ ነው ተብሎ ይጠረጠራል።

ተጠርጣሪው ነሐሴ 2025 በጣሊያን ተይዞ በኋላ ወደ ጀርመን ተላልፎ በተሰጠውና የቀድሞ የዩክሬን ወታደራዊ መኮንን ሰርጌ ኩዝኔትሶቭ በሚመራው ቡድን ውስጥ አባል እንደነበር ይታመናል።

ቁልፍ ዳራዎች፦

የሩሲያን የጋዝ ምርት ወደ አውሮፓ ለማድረስ የሚያገለግሉት የኖርድ ስትሪም 1 እና 2 የጋዝ ማስተላላፊያዎች መስከረም 26፣ 2022፤ መርማሪዎች የጥፋት ድርጊቶች ሲሉ በገለጹት ጥቃቶች ብልሽት ደርሶባቸዋል።

ቀደም ሲል የጀርመን ዐቃቤ ሕግ የጥፋት ድርጊቱ የተፈጸመው በዩክሬን የመንግሥት ተቋማት መመሪያ መሠረት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሶ፤ ተጠርጣሪዎቹን በጦር ወንጀል ከሷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0