የማዳጋስካር የመሬት ማስመለስ ሕግ ተመሳሳይ የቅኝ ግዛት ታሪክ ያላቸውን ሀገራት ሊያነሳሳ ይችላል - የማዳጋስካር ባለሥልጣን
15:14 19.08.2026 (የተሻሻለ: 15:24 19.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማዳጋስካር የመሬት ማስመለስ ሕግ ተመሳሳይ የቅኝ ግዛት ታሪክ ያላቸውን ሀገራት ሊያነሳሳ ይችላል - የማዳጋስካር ባለሥልጣን
በማዳጋስካር የመሬት ጉዳይ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ከመሆኑ አኳያ፤ ብሔራዊ ሀብቶችን ማስመለስ ለሉዓላዊነት ወሳኝ እርምጃ ነው ሲሉ የበማሶአንድሮ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ ጂሚ ራኒትራትሲሎ፤ የቀድሞ የቅኝ ግዛት መሬቶች ወደ መንግሥት መዛወራቸውን ያጸናውን የከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስመልከተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ ሕግ መሠረት እ.ኤ.አ ከሰኔ 26 ቀን 1960 ዓ.ም ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጋ ስም የተመዘገበና ወደ ማዳጋስካር ዜጋ ያልተዛወረ የትኛውም የመሬት ባለቤትነት መብት፤ በቀጥታ ወደ መንግሥት ባለቤትነት ይሸጋገራል።
ከከፍተኛ የሕዝብ ቁጥሯ አኳያ የማዳጋስካር የቅኝ ግዛት መሬቶችን የማስመለስ ጥረት፤ ተመሳሳይ ታሪካዊ እክል ያሉባቸውን "ሌሎች ሀገራት ሊያነሳሳ ይችላል" ሲሉ ባለሥልጣኑ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X