ኢትዮጵያ አካታች የስደተኞች ሥርዓት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት አጠናከረች
14:44 19.08.2026 (የተሻሻለ: 14:54 19.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ አካታች የስደተኞች ሥርዓት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት አጠናከረች
ከሁለት ወራት በፊት የስደተኞች እና የስደተኛ ተቀባይ ማኅበረሰቦችን ራስን መቻል እና የመቋቋም አቅም የማጠናከር ግብ አንግቦ የተቀረጸውን 'የማካተት' ፍኖተ ካርታ እንዲያስተባብር የተመረጠው መሪ ኮሚቴ፤ የፌደራል እና ክልላዊ ቢሮ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ደርሷል።
ቢሮው የተቀባይ ክልሎችን ልዩ ፍላጎት ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ አካባቢ መር ዕቅዶች እና የፍኖተ ካርታውን ትግበራ ይደግፋል።
ℹ በፍኖተ ካርታው መሠረት በኢትዮጵያ 1.2 ሚሊዮን ስደተኞች ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ዕቅዱም እነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎች በዘላቂነት በብሔራዊ የልማት ስትራቴጂ ውስጥ ማካተት ነው።
ኢትዮጵያ ከወዲሁ ስደተኞችን ከሀገሪቱ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መስጠት መጀመሯ የሚታወቅ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X