ሩሲያ እና ማሊ በሰሃራ-ሳኅል ቀጣና የሰላም ጥረቶችን ለማስተባበር ተስማሙ - ክሬምሊን
13:55 19.08.2026 (የተሻሻለ: 14:04 19.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ማሊ በሰሃራ-ሳኅል ቀጣና የሰላም ጥረቶችን ለማስተባበር ተስማሙ - ክሬምሊን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት እና የማሊ አቻቸው አሲሚ ጎይታ ረቡዕ የስልክ ውይይት ማካሄዳቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ አሲሚ ጎይታ ሩሲያ የማሊን ደህንነት ለማጠናከር እና ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት፤ በተለይም ትጥቅ ባነገቡ ጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመመከት ላደረገችው ጉልህ ድጋፍ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
▪ ፕሬዚዳንቶቹ "በማሊ እና በመላው የሰሃራ-ሳኅል ቀጣና መረጋጋትን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ቅንጅት ለመቀጠል" ተስማምተዋል።
▪ የስልክ ውይይቱ የተካሄደው በማሊ አነሳሽነት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X