በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በ47.3% የሞት ምጣኔ በታሪክ ሁለተኛው አስከፊ ወረርሽኝ ሆነ

© telegram sputnik_ethiopiaበኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በ47
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በ47 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.08.2026
ሰብስክራይብ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በ47.3% የሞት ምጣኔ በታሪክ ሁለተኛው አስከፊ ወረርሽኝ ሆነ

በኮንጎ አሁን ላይ በኢቦላ ወረርሽኝ 5 ሺህ 021 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ የ2 ሺህ 378 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኮንጎ እና በኡጋንዳ ግንቦት 7 የተከሰተው ይህ ወረርሽኝ፤ በአፍሪካ ታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ የሰው ህይወት የጠፋበት የኢቦላ ወረርሽኝ ሆኗል።

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስድስት ግዛቶች በወረርሽኙ የተጠቁ ሲሆን ኢቱሪ ግዛት ደግሞ የወረርሽኙ ዋና ማዕከል ሆናለች። ኡጋንዳ በበኩሏ የወረርሽኙን ማብቃት ሐምሌ 21 ቀን በይፋ አውጃለች።

ለዚህ ወረርሽኝ ምክንያት የሆነው የቡንዲቡግዮ የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ ክትባት አሁንም ሙከራ ላይ ይገኛል። የዓለም ጤና ድርጅት በኮንጎ የተቀሰቀሰውን ወረርሽኝ "ለዓለም የሚያሰጋ አጣዳፊ የሕዝብ ጤና ስጋት" ሲል ፈርጆታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0