የአሜሪካ ፍርድ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ እንዲነሳ ውሳኔ ሰጠ

© telegram sputnik_ethiopiaየአሜሪካ ፍርድ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ እንዲነሳ ውሳኔ ሰጠ
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ እንዲነሳ ውሳኔ ሰጠ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.08.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ ፍርድ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ እንዲነሳ ውሳኔ ሰጠ

ውሳኔው የጸረ-ስደተኞች ፖሊሲ የሚከተለው የትራምፕ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ፤ ሕጋዊነትን ሳይከተሉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገቡ የውጭ ሀገር ዜጎችን ከሀገሪቱ ለማስወጣት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።

በዚህም በጊዜያዊ የጥበቃ ሁኔታ (ቲፒኤስ) አማካኝነት በአሜሪካ የመቆየት እና ሥራ የመቀጠር መብት አግኝተው የነበሩ ከ5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሀገሪቱ እንዲወጡ ይገደዳሉ።

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መሥሪያ ቤት ውሳኔውን ተከትሎ በኤክስ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፤ "ሁሉም የቲፒኤስ ስረዛዎች አሁን ተግባራዊ ሆነዋል። የቲፒኤስ ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው ሰዎች አሁኑኑ ለቀው መውጣት አለባቸው። ይህን ካላደረጉ ወደ ሀገራቸው እናባርራቸዋለን " ብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0