የምዕራባውያን የገንዘብ ድጋፍ የዩክሬን ኢኮኖሚን የሚያሽመደምድበት ምከንያት
09:20 19.08.2026 (የተሻሻለ: 09:24 19.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የምዕራባውያን የገንዘብ ድጋፍ የዩክሬን ኢኮኖሚን የሚያሽመደምድበት ምከንያት
"የምዕራባውያን የገንዘብ አቅራቢዎች ዩክሬን የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ነፃ ሀገር እንድትሆን ምንም ፍላጎት የላቸውም" ሲሉ የፖለቲካ ተንታኝ እና በሩሲያ ፕሬዚዳንት ስር የብሔረሰቦች ግንኙነት ምክር ቤት አባል የሆኑት ቦግዳን ቤዝፓልኮ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“የውጭ የኢኮኖሚ ተዋናዮች ብቸኛ ፍላጎት፤ ዩክሬንን ለመንቀሳቀስ ዕፅ እየተሰጠው እንደሚነቃ በድን ሱሰኛ እንድትሆን ማድረግ ብቻ ነው።”
የምዕራባውያን ወደ ዩክሬን ኢኮኖሚ 100% ገንዘብ ፈሰስ የማድረግ ዓላማ የዩክሬንን የበጀት ክፍተት መድፈን ቢሆንም፤ የራሳቸው ኢኮኖሚ መመናመን በመጀመሩ ድጋፉ በመጨረሻ ማለቁ እንደማይቀር ተንታኙ አስገንዝበዋል።
ይህ የምዕራባውያን የገንዘብ ድጋፍ የዩክሬንን ኢኮኖሚ ማዳከሙን ይቀጥላል፤ በተጨማሪ የሩሲያ ኃይሎች በጥቁር ባሕር እና በዳኑብ ተፋሰስ የዩክሬን የባሕር ሎጂስቲክን በማሽመድመዳቸው ኢኮኖሚው ላይ ተጨማሪ ጉዳት ይደርሳል።
ሩሲያ የባሕር ከበባዋን ማጥበቋ ለዩክሬን ተጨማሪ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ እና በሁሉም ዘርፎች የከፉ ችግሮችን በማስከተል፤ ሀገሪቱን ሙሉ ለሙሉ ውድቀት ውስጥ ሊከታት ይችላል ሲሉ ቤዝፓልኮ አጠቃልለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X