ጋና እና ሩሲያ የሳኀል ቀጣናን በተመለከተ የደረሱት ስምምነት ‘የቅኝ አገዛዝ ጫናዎችን የሚያከስም’ ነው ሲሉ ኒጀራዊው ተንታኝ አወደሱ

ሰብስክራይብ

ጋና እና ሩሲያ የሳኀል ቀጣናን በተመለከተ የደረሱት ስምምነት ‘የቅኝ አገዛዝ ጫናዎችን የሚያከስም’ ነው ሲሉ ኒጀራዊው ተንታኝ አወደሱ

​ የጋና እና ሩሲያ ስምምነት በሳኅል የፀጥታ ትብብር ላይ የለውጥ ምዕራፍ ከፍቷል። ሞስኮ የራሷን ፍላጎት በግድ ከመጫን ይልቅ ሀገራቱ በሚያቀርቡት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ የምታደርግበት ነው ሲሉ የኒጀር 'ሲቲዝን አካዳሚ' ፕሬዝዳንት አዳሙ ኡማሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አበይት ነጥቦች፦

​🟠 ሩሲያ ቀደም ሲል ምዕራባውያን አጋሮች ይከተሉት ከነበረው "አሰገዳጅ" ሞዴል በተለየ "የሀገራቱን ፍላጎት መሠረት" አድርጋ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ልታቀርብ እንደምትችል ገልጸዋል።

​🟠 የፀረ-ሽብር ጥረቶችን በተመለከተ በቀጣናው ሀገራት መካከል ትብብር ማጠናከር በጣም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተንታኙ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ትብብሩ ይፋ የሆነው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከጋና አቻቸው ጋር ሰኞ በሞስኮ ከተወያዩ በኋላ ነው።

ላቭሮቭ የሳኅል ደህንነት፤ የሳኅል ሀገራት ጥምረት እና የኢኮዋስ አባላትን ጨምሮ ሁሉንም የሚመለከታቸው ሀገራት ትብብር እንደሚጠይቅ አስምረውበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0